ስለሚጥል በሽታ ምን ያክል ያውቃሉ


ስለሚጥል በሽታ ምን ያክል ያውቃሉ?


የሚጥል በሽታ ወይም ኤፕሊፕሲ (epilepsy) በአብዛኛው ሰዎችን የሚያጠቃ የአዕምሮ ወይም የነርቭ በሽታ ነው፡፡ ማንኛውንም ሰው በእድሜ፣ በፆታ፣ በቀለም፣ በዘር ወይም በማህበራዊ ደረጃ ሳይለያይ ክፉኛ የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሚጥል በሸታ በአዕምሮ የተዛባ እንቅስቃሴ ወይም በተጋነነ የነርቭ ስሮች (neuron) ረብሻ ምክንያት በሚፈጠር ድንገተኛ በሽታነው፡፡ ነው፡፡ ይህ ድንገተኛ በሽታ ወይም ማንቀጥቀጥ የተጠቂውን እንቅስቃሴና ንቃተ-ህሊና በእጅጉ ያዛባዋል፡፡
ምልክቶች
-ማንቀጥቀጥ
-የንቃተ ህሊና መዛባት
-ራስን መሳት
-የሳይኮሎዲካል ችግሮች እንደ ጭንቀት እና ፍርሀት
ምክንያቶቹ፡- የሚጥል በሽታ (Epilepsy) የበሽታው በመጣበት ምክንያት መሰረት በሁለት ይከፈላል፡፡
1.ምክኒያቱ የታወቀ (Symptomatic Epilepsy )፡- ከነዚህ ምክንያቶች መካከል፡
-የጭንቅላት ጉዳት
-የማጅራት ገትር በሽታ
-በደንብ ያልበለፀገ አዕምሮ
-ስትሮክ
-የአንጎል ዕጢ
-ከአልኮል ሱስ መውጣት ወይም ሕገ-ወጥ እፆችን መጠቀም
በህፃናት ላይ ደግሞ ያለው ምክንያት:
-በውልደት ጊዜ የሚፈጠር ጉዳት
-ከልጅነት ጀምሮ የሚኖሩ የአዕምሮ ችግሮች

 • በትኩሳት ምክንያት የሚፈጠር ማንቀጥቀጥ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
  2.ምክኒያቱ ያልታወቀ( Idiopathic Epilepsy )፡-ይህ ዓይነቱ ምንም ዓይነት የታወቀ ምክንያት የለውም፡፡ የችግሩ ምክንያት በዘር የተላለፈ ነው ተብሎ ብቻ ነው የሚገመተው፡፡ ስለዚህ ለበሽታው የታማሚው ዘረ-መሎች (Genes) ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡
  የተለያዩ የማንቀጥቀጥ ዓይነቶች በሁለት ዋና ዋና ምድቦች ተከፍለው እናገኛቸዋለን፡፡
  1.ሙሉ ማንቀጥቀጥ (Generalized Seizures)፡- ይህ አይነቱ የማንቀጥቀጥ አይነት ሁሉንም የአዕምሮ ክፍሎች (ግራና ቀኝ) እና አካባቢዎች የሚያጠቃ ነው፡፡ ከአንዱ ክፍል ተነስቶ ወደ ሌላው ክፍል በፍጥነት ይሰራጫል፡፡
  -የዚህ አይነቱ ማንቀጥቀጥ ያጠቃው ሰው የማልቀስ ወይም የሆነ ድምፅ ሊያሰማ እና ሰውነቱ ለተወሰነ ሴኮንዶች ደርቆ የመቅረት ከዚያም የእጅና የእግር መወራጨት ሊታይበት ይችላል፡፡
  -አይኖች በአብዛኛውን ጊዜ የተከፈቱ ናቸው፡፡
  -ተጠቂው ሰው የትንፋሽ እጥረት ሊገጥመው ይችላል፡፡
  -ተጠቂው ሰው ማንቀጥቀጡ ካቆመ በኋላ ከደቂቃት እስከ ሰዓታት ግራ ሊጋባ ይችላል፡፡
 1. ከፊል ማንቀጥቀጥ (Partial Seizures) ፡-በዚህን ወቅት የተወሰነ የአዕምሮ ክፍል ብቻ ተጠቂ ስለሆነ የተወሰነ የአካል ክፍል ነው ተጠቂ የሚሆነው፡፡ ይህ ማንቀጥቀጥ ከአዕምሮ ጉዳት፣ ከኢንፌክሽን፣ ከዕጢ ወይም ስትሮክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እንደሚያጠቃው የአዕምሮ ክፍል ሽፋን ምልክቶች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡
  -የእጃችንን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው የአዕምሮ ክፍል ከተጠቃ እጃችን የመወራጨት እንቅስቃሴ ያሳያል፡፡ እንዲሁ ሁሉ ሌሎች የአዕምሮ ክፍሎች ከተጠቁ በዛው መሠረት ሌሎች ምልክቶች ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል ልብስን መንጨት፣ ከንፈርን በጥፊ መምታት፣ አይን ማርገብገብ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
  -በከፊል ማንቀጥቀጥ ጊዜ ታማሚው ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሊያስታውሰው ይችላል፡፡
  ህክምናው (Treatment):
  የሚጥል በሽታ በህክምና ዕርዳታ ሊቆጣጠሩት የሚቻል በሽታ ነው፡፡ ነገር ግን ሊድን አይችልም፡፡ ሕክምናው በአብዛኛው ጊዜ መድሃኒት በመጠቀም የሚፈፀም ነው፡፡ እነዚህ መድሃኒት የማንቀጥቀጥ ድንገተኛ በሽታን ድግግሞሽ በመቀነስ የኑሮ ምቾትን ያሻሽላሉ፡፡ የመድሃኒቱ አወሳሰድ መጠን እንደታማሚው ሊለያይ ስለሚችል መጠኑ በሀኪም ሊጨመርና ሊቀነስ ይችላል፡፡
  ቀዶ ሕክምና ሌላው አማራጭ ነው፡፡ ይህ ግን የሚመከረው መድሃኒቱን ላልተቀበሉት ሰዎች ነው፡፡ በቀዶ ጥገና ወቅት ከስሜት ህዋሳት፣ ከአስተሳሰብና ከእንቅስቃሴ ጋር ያልተያያዘው የአዕምሮ ክፍል የማንቀጥቀጥ ችግርን ለመቆጣጠር ሊወገድ ይችላል፡፡
  ነገር ግን የማንቀጥቀጥ ችግሩ በአስፈላጊ የአዕምሮ ክፍል ላይ የሚነሳ ከሆነ ቀዶ ጥገና መካሄድ የለበትም፡፡

What's Your Reaction?

Cry Cry
0
Cry
Cute Cute
0
Cute
Damn Damn
0
Damn
Dislike Dislike
0
Dislike
Like Like
0
Like
Lol Lol
0
Lol
Love Love
0
Love
Win Win
0
Win
WTF WTF
0
WTF

ስለሚጥል በሽታ ምን ያክል ያውቃሉ

Choose A Format
Personality quiz
Series of questions that intends to reveal something about the personality
Poll
Voting to make decisions or determine opinions
Story
Formatted Text with Embeds and Visuals
List
The Classic Internet Listicles
Image
Photo or GIF
Gif
GIF format