በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ


በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው፣ ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት ያሬድ ዘሪሁን፣ ተስፋዬ ኡርጌ፣ የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩውሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል ጉደታ ኦላና እና ሌሎች ሦስት ተጠርጣሪዎች ናቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት።
ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ነው የቀረቡት።
ፍርድ ቤቱ በበለስ አንድ ፕሮጀክት ያለአግባብ ለሁለት የውጭ ድርጅቶች የግንባታ ውል በመስጠት ከፍተኛ የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረግ የተጠረጠሩት ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ ላይ ፖሊስ የቀረውን ምርመራ አጠናቆ እንዲያቀርብ 10 ቀን በመስጠት ለታሳስ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የአቃቢ ህግ ክስ በማደናቀፍ እና ተገቢ ያልሆነ ሃብት በማከማቸት ወንጀል የተጠረጠሩት በኮለኔል ጉደታ ኦላና ላይ ፖሊስ ከጀመረው ምርመራ በተጨማሪ ቀሪ ምርመራ አጠናቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ከህዳር 20 ጀምሮ በሚቆጠር የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዶ ለታሳስ 4 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከአዲስ የሜቴክ ሰራተኞች ጋር ተመሳጥሮ ከሁለት የውጭ ድርጅቶች 2 ሺህ 500 ትራክተር በድለላ በመግዛት ከ15 ሚሊየን በላይ ለግላቸው አውለዋል የተባሉት አቶ ረመዳን ሙሳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ፖሊስ የተጠረጠሩበትን ጉዳይም አስረድቷል፡፡
አቶ ረመዳን ሙሳ ላይ ፖሊስ ሦስት ምስክር የተቀበለ ሲሆን፥ የኦዲት እና ትራክተሮች ቆጠራ ለማድረግ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን ጠይቋል፡፡
ተከላካይ ጠበቃ በበኩላቸው ፖሊስ ሰነድ ሰብስቧል በዋስ ቢወጡ የሚፈጥሩት ጉዳት የለም ብለዋል፡፡
ሆኖም ፖሊስ በተከላካይ ጠበቃ የቀረበውን ዋስትና ተቋውሟል።
ፍርድቤቱም የፖሊስን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ለነገ ከሰዓት ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
እንዲሁም ፖሊስ በቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አቶ ያሬድ ዘሪሁን ላይ ከዚህ በፊት በተሰጠው ምርመራ ጊዜ ውስጥ በባለቤታቸው ወይዘሮ አዳነች ስም አገኘሁ ያለውን ሃብት ዘርዝሯል፡፡
በዚህም በባለቤታቸው ስም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤት እና በባለቤታቸው እናት በኢንቨስትመንት ፍቃድ የተመዘገበ 3 ሚሊየን 300 ሺህ ብር ካፒታል ማግኘቱን ገልጿል፡፡
እንዲሁም በኦሮሚያ ህብረት ባንክ በባለቤታቸው በአዳነች ስም 2 ሚሊየን 742 ሺህ ብር ማግኘቱንም ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡
በተጨማሪም ፖሊስ በእሳቸው ትዕዛዝ የሰው ህይወት ማለፉንና የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሶ፥ የሰው ማስረጃ ያገኘ በመሆኑ የ14 ቀን ተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል፡፡
የአቶ ያሬድ ጠበቃ በበኩላቸው ተጎጂዎቹ እነ ማን ናቸው፣ ተጎጂዎችን ፖሊስ ገና እያፈላለገ ባለበት ሁኔታ ሰነድ ያሸሻሉ ማለቱ ተገቢነት የለውም፣ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሃብት አከማችተዋል መባሉ በማስረጃ አልቀረበም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም አቶ ያሬድ ህመምተኛ ናቸው በዋስ እንዲወጡ ይፈቀድ ሲል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
ፖሊስ የዋስትና ጥያቄውን በመቃወም ለተለያዩ ተቋማት በሳቸውና ባለቤታቸው የተመዘገበ ሃብትን ተጨማሪ ለማጣራት ደብዳቤ መላኩንና ተጨማሪ ጥቆማም እየደረሰው መሆኑን ጠቅሶ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡
ፍርድቤቱም የምርመራ መዝገቡን ነገ ጧት ተመልክቶ ከሰዓት ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ፖሊስ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ካቀረበው ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪ ግለሰቦችን ያለአግባብ በማሰር በማሰቃየት እና በማስፈራራት እንዲሁም 6 ሚሊየን ብር እና 200ሺ የአሜሪካ ዶላር በመቀበል በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ሃብት በማከማቸት እንደጠርጠራቸው ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል፡፡
እንዲሁም ፖሊስ በአቶ ተስፋዬ ላይ ተጨማሪ በ6 ነጥቦች ምርመራ ለማድረግ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሏል፡፡
አቶ ተስፋዬ የስራ ኃላፊነቴ በጸረ-ሽብር መምሪያ ኃላፊ ነኝ እንጂ ሰዎችን የማሰርም ሆነ የማሰቃየት ኃላፊነት የለኝም ሲሉ ፍርድቤቱ ኃለፊነታቸውን እንዲመዘግብ ገልጸዋል፡፡
የአቶ ተስፋዬ ጠበቃም በሰኔ 16ቱ ቦምብ በማስተባበር ብሎ በፍርድቤት እየታየ በድጋሚ ፖሊስ ካለመያዣ ነው አሁን ይዞ የሚመረምረው ይህ ተገቢነት የለውም ብለዋል፡፡
ፖሊስ በበኩሉ ይህ ከሰኔ 16 ቦምብ ጋር የሚገናኝ አይደለም ምርመራው የተለየ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድቤቱም መዝገባቸውን ነገ ጠዋት መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለነገ ከሰዓት በይደር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው ላይ ፍርድቤቱ ፖሊስ ባለፈው በጽሁፍ ያቀረበውን የምርመራ ውጤትን በቃል አሰምቷል፡፡
ከትናንት በስቲያ በጽሁፍ የቀረበውን የፖሊስ ምርመራ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡
በሜጄር ጄነራል ክንፈና ወንድማቸው ኢሳያስ ላይ በቀረበ ምርመራ ጠበቃዎቹ የምርመራ መቋወሚያ አቅርበዋል፡፡
በዚህም በተራ ቁጥር 1፣ 2፣ 4፣ 7 እና 12 ላይ የተጠቀሰው የምርመራ ውጤት ከበፊቱ የተለየ አዲስ ነው፤ ይህም ፖሊስ እንደፈለገው በየጊዜው አዳዲስ ማቅረቡ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡
በአቶ ክንፈም ላይ በፊት አውሮፕላን ግዢ እና ህዳሴ ግድብ ምንጣሮ ተብሎ ነበር የቀረበው አሁን ላይ አዲስ ምርመራ መቅረቡ ተጠርጣሪዎችን አስቀድሞ ቅጣት እንዲወርዱና ንጹህ ሆነው የመገመት መብታቸውን የሚጎዳ ነው ፍርድቤቱ እልባት ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አመልክተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከመንግስት መስሪያ ቤት ለሚሰበሰብ ሰነድ ተጠርጣሪዎችን አስሮ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ አግባብነት የለውም፤ ከዚህ በተጨማሪ በጠቅላይ አቃቢህግ በደረሰው ጉዳት ኦዲት አድርጌ ጨርሿለው ብሏል፤ ለዚህም በሲዲ የተደገፈ ማስረጃ አለን ብለዋል ጠበቆቻቸው፡፡
በነ ክንፈ ላይ መንግስት አስቀድሞ መግለጫ የሰጠበት በተለይም ኦዲት ስራ ሰርቶ ምርመራ ማጠናቀቁን በገለጸበት ሁኔታ ፖሊስ ተጨማሪ እድመረምራቸው 24 ቀን ይፈቀድልኝ ማለቱ አግባብነት የለውም ፍርድቤቱ በመንግስት መግለጫ ላይ ያለንን ማስረጃችንን ይመልከትልን ሲሉ አመልክተዋል፡፡
ጠበቆቹ ሜቴክን ከማስታወቂያ ጋር በተያያዘ ለቀረበው ክስ ድርጅቱ መተዋወቅ አልነበረበትም ወይ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ድርጅቱ ከሚያገናኘው ስራ ጋር በተያያዘ እንደወንጀልም ሊቀርብ አይገባም ብለዋል፡፡
አቶ ኢሳያስም ቢሆኑ የፕሮግራም ኃላፊ እንጂ የፓወር ተከላ ፕሮጀክት ያለአግባብ ሰጥተዋ መባሉ አግባብነት የለውም ሲሉ ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡
አቶ ክንፈ ላይም በተመሳሰይ ሜቴክ ከተቋቋመ ጀምሮ የተሰራ ስራን በማይመለከታቸው ጉዳይ እሳቸውን ተጠያቂ ለማድረግ ለቀሪ ምርመራ ተብሎ መቅረቡ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

What's Your Reaction?

Cry Cry
0
Cry
Cute Cute
0
Cute
Damn Damn
0
Damn
Dislike Dislike
0
Dislike
Like Like
0
Like
Lol Lol
0
Lol
Love Love
0
Love
Win Win
0
Win
WTF WTF
0
WTF

በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

Choose A Format
Personality quiz
Series of questions that intends to reveal something about the personality
Poll
Voting to make decisions or determine opinions
Story
Formatted Text with Embeds and Visuals
List
The Classic Internet Listicles
Image
Photo or GIF
Gif
GIF format