አሜሪካ ፣ካናዳና ሜክሲኮ አዲስ ነፃ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ


አዲስ አበባ፣ህዳር 22፣2011 አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በትናንትናው ዕለት አዲስ ነፃ የንግድ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለፀ።
ሀገራቱ ስምምነቱን የፈፀሙትም ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በመካሄድ ላይ ባለው የቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት የጎንዮሽ ስብሰባ ወቅት ነው ተብሏል።
ስምምነቱንም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና የሜክሲኮው ፕሬዚዳንት ኤንሪኬ ቴኛ ኒኤቶ ተፈራርመውታል።
ይህ አዲስ ነፃ የንግድ ስምምነትም ከዚህ በፊት “ናፍታ” በመባል የሚታወቀውን የሰሜን አሜሪካ ነፃ የንግድ ሥምምነት የሚተካ ነው ተብሏል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱ የሶስቱ ሀገራት የጋራ የንግድ ልውውጥን በይበልጥ ለማጠናከር ከማስቻሉም በላይ ለሌሎች ሀገራትም አርአያ የሚሆን ስምምነት ሲሉ አወድሰውታል።
አሜሪካ ከዚህ በፊት “ናፍታ” ተብሎ በሚጠራው ነፃ የንግድ ስምምነት ላይ የነበሩ የንግድ ህግና ደንቦች ይሻሻሉ ዘንድ ከዓመት በፊት ጀምራ ሀገራቱን ስታወያይ መቆየቷንም አክለዋል።
በ 2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ወቅትም የሰሜን አሜሪካን ነፃ የንግድ ስምምነት እንደገና በማደስ አዲስ ታሪክ እንደሚያስመዘግቡ ቃል መግባታቸውን አስታውሰዋል።
አዲሱና በአይነቱ ዘመናዊ የተባለው ይህ ስምምነት በካናዳ ፣አሜሪካና ሜክሲኮ መካከል የሚደረገውን ቀጠናዊ የንግድ ልውውጥ በማሳለጥ ለሀገራቱ ነጋዴዎችም አዲስ የለውጥ ተስፋን የሚሰንቅ እንደሚሆን ነው የተነገረው።
በዚህ ስምነት ላይ ከፀደቁ አዲስ ነፃ የንግድ ስምምነቶች ውስጥም አብዛኛዎቹ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

What's Your Reaction?

Cry Cry
0
Cry
Cute Cute
0
Cute
Damn Damn
0
Damn
Dislike Dislike
0
Dislike
Like Like
0
Like
Lol Lol
0
Lol
Love Love
0
Love
Win Win
0
Win
WTF WTF
0
WTF

አሜሪካ ፣ካናዳና ሜክሲኮ አዲስ ነፃ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

Choose A Format
Personality quiz
Series of questions that intends to reveal something about the personality
Poll
Voting to make decisions or determine opinions
Story
Formatted Text with Embeds and Visuals
List
The Classic Internet Listicles
Image
Photo or GIF
Gif
GIF format