የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ዝምተኛው የኩላሊት ህመም


የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ዝምተኛው የኩላሊት ህመም


ኩላሊት ብዙ ትኩረት ያልሰጠነው ዋነኛ የሰውነታችን ክፍል ነው ።የኩላሊትም ስራ ማቆም ይገድላል ። የኩላሊት ተግባር
1 ሽንት ማጣራት
2.በሰውነታችን ሴሎች ውስጥና ከምንመገባቸው ምግቦች የሚፈጠሩ እጅግ ጎጂ የሆኑ መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን ማስወገድ ።
3 ደም በማጣራት በሰውነታችን ውስጥ የማያስፈልጉ ነገሮችን በሽንት መልክ ማስወገድ ሌላው ነው።
4 .በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀመ አላስፈላጊ ውሃን ማስወገድ እና የካልሺየምና የፎስፌት ማዕድናት መጠንን መቆጣጠርም ሌላኛው ስራው ነው።
5 .የደም ዝውውርን የሚያፋጥኑና የቀይ ደም ህዋስ መመረት ሂደትን የሚጨምሩ ሆርሞኖችንም ያመርታል።
ከላይ 5 ቱን ነጥቦች እንደ ምሣሊ ላንሣ እንጂ እጅግ በርካታ ተግባራት የሚከውነው ኩላሊት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥልና ስራውን በተገቢው መንገድ እንዲያከናውን
ቀጥሎ በአጭሩ የተብራሩ ጉዳዮችን ማጤን ይገባል ።

 1. በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ –
  በቂ ውሃን አለመጠጣት የኩላሊት ሥራ የሆነውን አላስፈላጊ ቆሻሻን ከሰውነታችን ማስወገድ በሚገባ እንዳያከናውን ስለሚያደርግ ቆሻሻው በኩላሊታችን ውስጥ ተከማችቶ ጉዳት እንዲያስከትል ያደርጋል፡፡
 2. ሽንትን መቋጠር –
  የውሃ ሽንትን ማስወገድ በሚገባን ጊዜ ሳናስወግድ የምንይዘው ከሆነ እና ይህን ተግባር የምናዘወትር ከሆነ የሽንት ፊኛችንም ሆነ ኩላሊታችንን አደጋ ላይ የምንጥል መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡
 3. ጨው የበዛበትን ምግብ መውሰድ
  – ጨዋማ ምግቦችን መመገብ የኩላሉትን ጨውን (sodium) ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራ ጫና እንዲበዛበትና ሲቆይም ለችግር እንዲጋለጥ ያደርጋል፡፡
 4. ካፊን በብዛት መውሰድ –
  በሚጠማን ጊዜ ውኃ ከመጠጣት ይልቅ ለስላሳ መጠጦችን እንደ ጥም ቆራጭነት እንጠቀማለን፡፡ ካፌን የደም ግፊት መጠናችንን በመጨመር ኩላሊትን ይጎዳል፡፡
 5. ሕመም ማስታገሻ አለአግባብ መውሰድ –
  ቀላል ለሚባል የሕመም ስሜት ሕመም ማስታገሻዎችን መውሰድ አላስፈላጊ እና አልፎ ተርፎም ከባድ የሆነ የኩላሊት ጉዳትን ሊያደርስ ይችላል፡፡
 6. የአልኮል መጠጥን በብዛት መጠጣት –
  ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥን ማዘውተር የኩላሊት ችግር ያስከትላል፡፡
 7. ሲጋራ ማጤስ –
  ለኩላሊት መድረስ የሚገባውን የደም መጠን ና አየርን ስለሚቀንስ ሲጋራ ማጤስ እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡
  8 .ፕሮቲን የበዛባቸው ምግቦች
  ፕሮቲን ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም፥ ቀይ ስጋና የፕሮቲን መጠናቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን በተደጋጋሚ መመገብ ለኩላሊት በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል።
  9 .አልኮል
  የአልኮል መጠጦችን አብዝተን በምንጠጣበት ወቅት ዩሪክ አሲድ በኩላሊታችን ቱቦ ይከማቻል። ይህም ኩላሊታችን የተለመደ ተግባሩን እንዳያከናውን እክል ይፈጥራል።
 8. ህመሞችን ቸልን ማለት
  በቀላሉ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን እንደ የአባላዘር በሽታ ጉንፋን ና የሽንት ቱቦ ህመሞችን ቸል ማለት
  ኩላሊታችን የተለመደ ተግባሩን እንዳያከናውን ያደርጋል
  ስለዚህ ለኩላሊቶቻችን ጥንቃቄ እያደረግን ኩላሊታችንን ከብልሽት እናድን እላለሁ ።

What's Your Reaction?

Cry Cry
0
Cry
Cute Cute
0
Cute
Damn Damn
0
Damn
Dislike Dislike
0
Dislike
Like Like
0
Like
Lol Lol
0
Lol
Love Love
0
Love
Win Win
0
Win
WTF WTF
0
WTF

የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ዝምተኛው የኩላሊት ህመም

Choose A Format
Personality quiz
Series of questions that intends to reveal something about the personality
Poll
Voting to make decisions or determine opinions
Story
Formatted Text with Embeds and Visuals
List
The Classic Internet Listicles
Image
Photo or GIF
Gif
GIF format