ድረስ ምታት ለራስ ምታት ልስጡ የሚችሉ ህክምናዎች


የራስ ምታት/ Headache
ለራስ ምታት ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች
ለማይግሬይን አይነት የራስ ምታት ህመሙን/ስቃይን ሊያስታግሱ የሚችሉ መድሃኒቶች
• ጥሩ ዉጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ የህመም ማስተጋሻ መድሃኒቶችን ህመሙ እንደጀመረዎ ወዲያዉ መዉሰድ ይገባል፡፡ ህመሙ ባለበት ወቅት መድሃኒትዎን ወስደሁ ዕረፍት ቢያደርጉ ወይም ጨለማ ክፍል ውስጥ እንቅልፍ ቢተኙ ሊረዳዎት ይችላል፡፡
• የህመም ማስታገሻ፡- አስፒሪን፣አይቡፕሮፌንና አሴታሚኖፌን የመሳሰሉት መለስተኛ የማይግሬይን ህመሞችን ሊያስታግሱ ይችላሉ፡፡
• እንደ ትሪፕታነስ፣ኢርጎትስ፣ኦፕዮይድስ፣የትዉከት ማስታገሻ እንክብሎችና ጉሉኮኮርቲኮይድስ የመሳሰሉት መድሃኒቶችም ለህክምናዉ አገልግሎት ይዉላሉ፡፡
የማይግሬይን ራስምታትን ለመከላከል የሚሰጡ ህክምናዎች ( Preventive medications)
እነዚህ መድሃኒቶች የሚታዘዝልዎ
1) የስቃይ ማስታገሻ መድኃኒቶች ህመሙን መስታገስ ካልቻሉ
2)ከፍተኛ የሆነ ህመም በወር አራቴና ከዚያ በላይ ካለዎ
3) የህመሙ ስቃይ ከ12 ሰዓታት በላይ የሚቆይ ከሆነ እና
4) የራስ ምታቱ ተያያዥ የሆነ እንደ መደንዘዝ፣የጡንቻዎች መስነፍና የራስምታቱ ሊመጣ ሲል የሚሰሙት፣የሚያዩት ወይም የሚሸትዎ ነገሮች ካሉ፡፡
እነዚህ መድሃኒቶች የራስምታቱ የሚመጣበትን ፍጥነት፣ ደረጃና የሚቆይበትን እርዝማኔ የሚቀንሱ ሲሆን በተጨማሪም የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶቹን የመስራት አቅም ይጨምራሉ፡፡ መድሃኒቶቹ በየቀኑ ሊወሰዱ ይችላሉ፤አለበለዚያም ህመሙን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ነገሮች በሚቃረቡበት ወቅት (የወር አበባ ሊመጣ ሲል) ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ መድሃኒቶች ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ
• ካርዲዮቫስኩላር ድረግስ፡-ፕሮፕራኖሎል፣ሜቶፕሮል
• አንታይዲፕሬሳንት፡- አሚትሪፕትሊን
• ለሚጥል ህመም ሊሰጡ ከሚችሉ መድሃኒቶች እንደ ቫልፑሬት ሶዲያም ያሉት ይገኛሉ፡፡
የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና
ለራስዎ የሚያደርጉት እንክብካቤ የራስ ምታትን የህመም ስሜትዎን ሊቀንስ ይችላል፡፡
• የጡንቻ ማፍታታት እንቅስቃሴ ማድረግ/ muscle relaxation exercises /፡- ይህን ማድረግዎ ህመምዎን ሊቀንስልዎ ይችላል፡፡ ይህም ዮጋና ሜድቴሽን የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
• በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡- በእያንዳንዱ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ለማግኘት መቻል ነዉ እንጂ ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ መተኛት የለብዎትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ወደ አልጋ ለእንቅልፍ የሚሄዱበትና ሲነጋ የሚነሱበት ሰዓት ተመሳሳይ ቢሆን ይመረጣል፡፡
• እረፍት ማድረግና ዘና ማለት፡- ያለዎት ራስምታት ሚግሬይን ከሆነ ከተቻለ ፀጥ ያለና ጨለማ ክፍል ቢያርፉ ይመረጣል፡፡ በረዶ በጨርቅ አድርገሁ በማጅራትዎ ስር ያድርጉና በመጠኑ ህመም በሚሰማዎ የጭንቅላትዎ አካባቢ ጫን ጫን ያድርጉ::
• ሁሌ የራስምታት ደያሪ( diary) መያዝ/መመዝገብ፡- ይህን አዘዉትሮ ማድረግ የራስምታት ህመምዎን ምን እንደሚያስነሳብዎና የትኛዉ ህክምና እንደሚያሽልዎ ለማወቅ ይረዳል፡፡

What's Your Reaction?

Cry Cry
0
Cry
Cute Cute
0
Cute
Damn Damn
0
Damn
Dislike Dislike
0
Dislike
Like Like
0
Like
Lol Lol
0
Lol
Love Love
0
Love
Win Win
0
Win
WTF WTF
0
WTF

ድረስ ምታት ለራስ ምታት ልስጡ የሚችሉ ህክምናዎች

Choose A Format
Personality quiz
Series of questions that intends to reveal something about the personality
Poll
Voting to make decisions or determine opinions
Story
Formatted Text with Embeds and Visuals
List
The Classic Internet Listicles
Image
Photo or GIF
Gif
GIF format